ሰላም!

አሳክተውታል!

እርስዎ ከእኛ መዝገብ የ QR ኮዱን ቃኝተዋል (ስካን አድርገዋል) ወይም በድንገት ወደዚህ ድብቅ ድረገጽ ሳያስቡት መጥተዋል። ዋናው ነገር እዚህ መገኘትዎ ነው!

ይህ ገጽ በሚኖሩባቸው ማኅበረሰቦች ውስጥ ለውጥ ለማምጣት በየቀኑ በመደበኛነት ድምፅ ስለሚሰጡ ሰዎች እውነተኛ ምሳሌዎችን ያቀርባል። ከዚህ በታች ያለውን ይዘት ለመመልከት ትንሽ ጊዜ ይውሰዱ እና የሆነ ነገር ለእርስዎ ስሜት ይሰጥዎት እንደሆነ ያረጋግጡ። ከዚህ በተጨማሪ የሲቪክ ማኅበረሰብን ኃይል የሚያሳዩ  ተጨማሪ ምሳሌዎችን ማግኘት የሚችሉባቸው አገናኞች (ሊንኮችን) ከግርጌ ላይ ይገኛሉ።

(እናም አንድ ነገር አይርሱ፣ ለጓደኞችዎ ወይም ለጠላቶችዎ በ8 የተለያዩ ቋንቋዎች የጽሑፉን ቅጂዎች መግዛት ይችላሉ!)

1930s
The Brotherhood of Sleeping Car Porters Win A Union, 1937

የስሊፒንግ ካር ፖርተርስ ወንድማማቾች /Brotherhood of Sleeping Car Porters/ የሠራተኛ ማኅበር፣ 1937 ክርክርን አሸነፈ

በኤ ፊሊፕ ራንዶልፍ ( A. Philip Randolph) የተባለ ኅብረተሰባዊ አደራጅ እየተመሩ፣ በ19ኛው ክፍለ ዘመን ማብቂያ እና በ20ኛው ክፍለ ዘመን መባቻ ላይ በአሜሪካ ውስጥ በጣም ብዙ ቁጥር ያላቸውን ጥቁር ሠራተኞች በመቅጠር ግንባር ቀደም በሆነው በሰሜን አሜሪካ የምድር ባቡር ውስጥ የሚሠሩ አገልግሎት ሰጪ ሠራተኞች በፑልማን ኩባንያ (Pullman Company) የሠራተኛ ማኅበራቸው ዕውቅና እንዲያገኝ ለማድረግ 12 አታካች ዓመታትን ከወሰደ ትግል በኋላ ውጤታማ ሆነዋል። ከዚህ በኋላ፣ በመጀመሪያ የ20ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ BSCP በጣም ተሰሚነት ካላቸው ኃይለኛ የጥቁር ሠራተኞች ማኅበራት መካከል አንዱ ለመሆን ችሏል።

ስለ ወንድማማቾች (Brotherhood) ተጨማሪ መረጃ ያግኙ

1960s

migrant worker holding megaphone

የ1960ዎቹ የዩናትድ ፋርም ዎርከርስ ግሬፕ /United Farm Workers Grape/ ሥራ ማቆም አድማዎች

ከ1962 ጀምሮ፣ መጠነ ሰፊ የሆነ ምጣኔ ሃብታዊ እና መሠረታዊ የሠራተኛ መብቶችን ለማስከበር እንዲቻል ዐሥርት ዓመታትን የፈጀ የሥራ ማቆም አድማዎችን ለማድረግ እና ተቃውሞዎችን ለማሰማት ሴዛር ሻፌዝ (Cesar Chavez) እና ዴሎረስ ሂዩርታ (Delores Huerta) የተባሉ የሠራተኛ ማኅበር መሪዎች በካሊፎርኒያ እና በምዕራብ አሜሪካ ውስጥ ያሉትን የእርሻ ሠራተኞች ተቀላቀሏቸው። የ UFW ዘመቻ የሮበርት ኬኒዲን (Robert Kennedy)፣ የዎልተር ረቱር (Walter Reuther) እና ማርቲን ሉተር ኪንግን (Martin Luther King) ትኩረትና ለመሳብ ቻለ፤ እና በ1971 በወይን እርሻ፣ በወይን ጠጅ ፋብሪካዎች እና ሌላው ሳይቀር በአንዳንድ የአታክልት አምራቾች ዘንድ ለውጦች እንዲደረጉ ምክንያት ሆነዋል እንዲሁም አዳዲስ 70,000 አባላትን ለማግኘት ችለዋል።

የዩናትድ ፋርም ዎርከርስ ግሬፕ /United Farm Workers Grape/ የ1960 የሥራ ማቆም አድማዎች የበለጠ ይወቁ

1970s

people laying down in front of bus to protest lack of wheelchair accessibility

ለአቴንዳንት ፕሮግራም ቱደይ የአሜሪካ አካል ጉዳት ያለባቸው ሰዎች እንቅስቃሴ /American Disabled for Attendant Programs Today (ADAPT)/ ዐመፅ፣ 1978

ግራ የተጋባው የጤና እንክብካቤ ሰጪ ሠራተኛ እና የፐሪስቢቴሪያን ቤተክርስቲያን ካህን የሆነው ዌድ ብላንክ (Wade Blank) በ1970ዎቹ ዴንቨር እና ሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች አጋጥሞ በነበረው የኢኮኖሚ ቀውስ ወቅት ምን ያክል አካል ጉዳተኞች የተሟላና ሰብአዊ ክብራቸውን የማይነካ ሕይወት እንዲኖሩ ከማገዝ ወደ ኋላ እንዳፈገፈጉና እንዳልቻሉ አስተዋለ። የዴንቨር አካል ጉዳተኛ ማኅበረሰብን ለማቋቋም እንዲያስችለው የአትላንቲስ ማኅበረሰብን መሠረተ፣ ሆኖም ግን ብላንክ (Blank) እና የማኅበረሰቡ አባላት ይህ በቂ እንዳልሆነ በመገንዘብ ADAPT የተባለውን ማኅበራቸውን አቋቋሙ። በ 70ዎቹ መጨረሻ ላይ፣ ADAPT በዴንቨር ውስጥ የሕዝብ ትራንስፖርት ተደራሽነት ለአካል ጉዳተኞች አለመኖርን ለመቃወም ዐመፅ ጀመሩ፤ እነዚህ በአንድ ክልል ውስጥ የተደረጉ ተቃውሞ እንቅስቃሴዎች በቅርብ ጊዜ የአሜሪካ ታሪክ ትልቅ ከሚባሉት የሲቪል መብት አዋጆች መካከል አንዱ የሆነው የአሜሪካ የአካል ጉዳት ያለባቸው ሰዎችን የተመለከተ ሕግ እንዲወጣ ምክንያት ሆነዋል።

ስለ የ ADAPT የተቃውሞ እንቅስቃሴ፣ 1978 የበለጠ ይወቁ

1980s

black and white photo Japanese American Citizens League in 1970s

የጃፓን ዝርያ ያላቸው አሜሪካዊ ዜጎች ሊግ ወደ አገራቸው እንዲባረሩ የተወሰነውን ውሳኔ፣1988 አስቀለበሱ

በ1930ዎቹ የጦርነት ወቅት ጭንቀትና ወከባ ምክንያት በመገፋፋት የአሜሪካ መንግሥት የጃፓን ዝርያ ያላቸውን ስደተኛ ማኅበረሰቦችን ብቻ ሳይሆን የኒሴይ ጃፓናዊ አሜሪካዊ (Nisei–Japanese-American) ዜጎችን ጨምሮ ከካሊፎርኒያ እና ከዌስት ኮስት እንዳለ በመሰብሰብ በኮሎራዶ እና በሌሎች በምዕራብ ያሉ የተለያዩ ቦታዎች ላይ በተዘጋጁ ጊዜያዊ ካምፖች ውስጥ በግድ እንዲሰባሰቡ አደረገ። በፌዴራሉ መንግሥት በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቅ እና እንዲሁም እነርሱን እና ቤተሰቦቻቸውን ከአገር የማባረሩ እርምጃ ውስን እንዲሆን ለማድረግ የጃፓናዊ-አሜሪካዊያን ዜጎች ሊግ፣ እንቅስቃሴ ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት ማብቂያ በኋላ እንደገና ተጀመረ፤ ተደራጀ፤ የተለያዩ ሕዝባዊ ንግግሮች ተደረጉ እንዲሁም ሕግ አውጪዎችን ስለ ጉዳዩ ለማሳመን የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ተደረጉ።

ስለ የጃፓን ዝርያ ያላቸው አሜሪካዊ ዜጎች ሊግ ወደ አገራቸው እንዲባረሩ የተወሰነውን ውሳኔ ስለማስቀልበስ በቀጣይ ድኅረገጽ ላይ የበለጠ ይወቁ

men holding a banner that says Fighting for Our Lives

የዴንቨር መርሆዎች፣ 1983

በ1987 ፀደይ ወራት፣ የኒውዮርክ ነዋሪ የሆነው ደራሲ ላሪ ክራመር (Larry Kramer) እና ቁጥራቸው ወደ 300 የሚደርሱ ሌሎች የማኅበረሰብ አንቂዎች የሕዝብ ጤና ፖሊሲዎች እንዲወጡ ወይም እንዲቀየሩ ለማድረግ እና ስለ ተላላፊው በሽታው ግንዛቤ ለማስጨበት በቀጥታ እንቅስቃሴ የሚያደርግ AIDS Coalition to Unleash Power (ACT UP) የተባለ የኤድስ ነክ ማኅበራትን የሚያስተባብር ማኅበር አቋቋሙ። ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ኤድስን በተመለከተ በአገሪቱ ውስጥ በታችኛው ደረጃ ይደረግ የነበረ የማኅበረሰብ ማንቃት ሥራ ቀደም ብሎ ጠንካራ መሠረትን እና ተቀባይነት እያገኘ በመሄድ ላይ ነበር። የዚህ የመጣው የአመለካከት ለውጥ አንዱ ማሳያ አብነት በ 1983 በጋ ወቅት በዴንቨር የተደረገው የወንድና ሴት ግብረሰዶማውያን የጤና ኮንፍራንስ ላይ የተፈጠረው ነገር ነው። “የዴንቨር መርሆዎች” በተባለው ማኒፌስቶ በኮንፍራንሱ ላይ የተሳተፉ የማኅበረሰብ አንቂዎች በመላው አገሪቱ በሚገኙ በእያንዳንዱ ትላልቅ ከተሞች ውስጥ ከኤድስ ጋር የሚኖሩ ሰዎችን የያዙ ቡድኖችን ያካተተ “ብሔራዊ ከኤድስ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ማኅበር” የተባለውን አውታረ መረብ ወጠኑ። ከኮንፍራንሱ በኋላ፣ በዴንቨር ውስጥ ከኤድስ ጋር የሚኖሩ ሰዎች የአካባቢው ተወካዮች በጤና እና ከኤድስ ጋር በተገናኙ ጉዳዮች ላይ ግዛቱ ሕጎችን እንዲያወጣ የመሪዎችን ድጋፍ ለማግኘት ንቁ እንቅስቃሴ በማድረጋቸው በከተማው ውስጥ በሽታውን በተመለከተ ከፊት ለፊት ተጠቃሽ አካል ለመሆን በቅተዋል።

ስለ ዴንቨር መርሆዎች በቀጣይ ድኅረገጽ ላይ የበለጠ ይወቁ

2010s

striking teachers holding signs that say "on strike for our students"

የንግድ ድርጅት የዴንቨር ትምህርት ቤቶችን እንዳይቆጣጠር ለማድረግ መምህራን የሥራ ማቆም አድማ አደረጉ፣ 2019 (በተቃውሞው ላይ ተማሪዎችም ተሳታፊ ነበሩ)

የመማሪያ ክፍሎች እንዲጨናነቁ፣ ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ፣ እና የደሞዝ ማሻሻያ እንዳይደረግ ማንቆ የሆነው ዐሥርት ዓመታትን የወሰደው በዴንቨር ትምህርት ቤት ቦርድ ውስጥ እና ውጪ ባሉ የግል የንግድ ድርጅቶች ቁጥጥር ሥር የማድረግ ሂደት የተነሣ መምህራን ሥራቸውን ጥለው ወጡ። ይህ የሥራ ማቆም አድማ የደሞዝ ጭማሪን ጥያቄ መልስ ማስገኘት ብቻ ሳይሆን በመማሪያ ክፍላቸው ውስጥ በበለጠ ነጻነት ማስተማር እንዲችሉ አድርጓቸዋል፣ በፊት ግን “ለፈተና ብቻ እንዲያስተምሩ” ይደረጉ ነበር። የዴንቨር መምህራን ተቃውሞዋቸውን በጋራ በማሰማት ማሸነፍ ከመቻላቸው ባሻገር ከበርካታ ተማሪዎቻቸው ጋር፣ በወቅቱ እንቅስቃሴው በሰላማዊ መልክ ከደገፉት ጋር ጠንካራ የሆነ ኅብረትን ለመመሥረት ችለዋል።

ስለ 2019ኙ የዴንቨር መምህራን የሥራ ማቆም አድማ በቀጣይ ድኅረገጽ ላይ የበለጠ ይወቁ

protesters for Universal Housing & Rent Control

የኒው ዮርክ ቤት ተከራዮች በኒው ዮርክ ቤት አከራዮች ላይ ክስ በመመሥረት አሸነፉ፣ 2019

በአንድ በኩል ሪል እስቴቶች እና ትላልቅ ቤት አከራዮች በሌላ በኩል የኒው ዮርክ ቤት ተከራዮች በሌላ አነጋገር ሁሉም በኒው ዮርክ የሚኖር ሰው መካከል ከሃያ ዓመታት ለበለጠ ትግል ከተደረገ በኋላ የቤት ኪራይ ቁጥጥርን ጨምሮ በርካታ ሥር ነቀል ቋሚ የቤት ተከራዮችን መብቶች የሚያስከብሩ ተከታታይ ሕጎች እንዲወጡ ሆኗል። ሥራው የተሠራው በሁሉም በኒው ዮርክ ውስጥ በሚኖር ተከራይ ቢሆንም እንቅስቃሴውን ያደራጁት፣ እንደ ኒው ዮርክ ቻፕተርስ ኦፍ ዘ ዴሞክራቲክ ሶሻሊስት አሜሪካ (New York chapters of the Democratic Socialists of America) እና ወደ 100 የሚጠጉ አባላት ያሉት በአንድ ሰፈር፣ አንድ ሕንፃ ውስጥ የተደራጀ የሃውሲን ጀስቲስ ፎር ኦል (የመኖሪያ ቤት ፍትሕ ለሁሉም) የተባለ የተከራዮች ቡድን የመሳሰሉ ቡድኖች ተከራዮችን ለመብቶቻቸው ለበርካታ ዓመታት በጽናት መታገል ብቻ ሳይሆን ጥያቄዎቻቸው ከመብት ማስከበር ትግልነት አልፈው በሕግ ደረጃ ተረቀው በስቴት ደረጃ እንዲፀድቁ ምክንያት ሆነዋል።

ስለ 2019ኙ የኒው ዮርክ ተከራዮች እና አከራዮች ውዝግብ በቀጣዩ ድኅረገጽ ላይ የበለጠ ይወቁ

2020s

indigenous people standing in a row

ስታንዲንግ ሮክ ትራይብስ /Standing Rock Tribes (እና አጋሮቻቸው) DAPL እንዲቆም አስደረጉ፣ 2020

ከ2014 ጀምሮ እስከ 2017 መጨረሻ ድረስ፣ ቁጥራቸው ከ5,000 የሚበልጡ ሰዎች በነባር ነዋሪዎች መኖሪያ ሰፈሮች ውስጥ የሚያልፍ ርዝመቱ 8,000 ማይል የሆነ የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ መዘርጋት ለመቃወም ስታንዲንግ ሮክ (Standing Rock)፣ በደቡብ ዳኮታ (South Dakota)ተሰባሰቡ፤ የነባር ነዋሪዎች መሪዎች በ1851ዱ የፎርት ላርሚን (Fort Laramie) ስምምነት መሠረት መሬቱ የእነርሱ እንደሆነ እና የአሜሪካ መንግሥት ይህን ስምምነት እየጣሰ እንደሆነ አሳወቁ። በ2020 መባቻ ላይ፣ ተቃውሞ የሚያሰሙት ጎሣዎች ፕሮጄክቱ “ሥር ነቀል በሆነ ሁኔታ ከአካባቢው ጋር የሚጣጣም ስለመሆኑ ክለሳ” እንዲደረግበት የሚያስገድድ ውሳኔ እንዲወሰን በማስደረግ የቧንቧው ዝርጋታ ሥራ (ለጊዜው) እንዲቆም አስደርገዋል።

ስለ ስታንዲንግ ሮክ ጎሣዎች (Standing Rock Tribes)ን በቀጣይ ድኅረገጽ ላይ የበለጠ ይወቁ

protesters for Universal Housing & Rent Control

የዲትሮይት (Detroit) አውቶቡስ ሾፌሮች በ2020ው ዓለም አቀፍ ወረርሺኝ ወቅት መብታቸውን አስከበሩ

የኮሮና ቫይረስ ዓለም አቀፍ ወረርሺኝ በጀመረባቸው የመጀመሪያዎቹ ወራት፣ የግል ንጽሕና እና ደኅንነት መጠበቂያ (PPE) እና የአፍና አፍንጫ ጭንብል ከከተማው መስተዳደር ማግኘት እንዲችሉ በዴትሮይት (Detroit) ውስጥ በማኅበራቸው የተደራጁ የአውቶቡስ ሾፌሮች የ24 ሰዓት የሥራ ማቆም አድማ አደረጉ። “ሲወያዩበት ነበር፣ በመጨረሻውም ወደ ሥራ እንደማይገቡ አንድ ላይ ወሰኑ። ወደ እኛ ደወሉ እና ከእነርሱ ጎን እንድንቆም ጥያቄ አቀረቡልን፤ እኛም በጥያቄዎች መሠረት ማድረግ የነበረብንን አደረግን” ይላሉ የማኅበሩ ምክትል ፕሬዝዳንት ዊሊ ሚቺል (Willie Mitchell)።

ስለ የዲትሮይት (Detroit) አውቶቡስ ሾፌሮች በ2020ው ዓለም አቀፍ ወረርሺኝ ወቅት መብታቸውን ስለ ማስከበራቸው በቀጣዩ ድኅረገጽ ላይ የበለጠ ይወቁ

በታሪክ ውስጥ ሰዎች በየቀኑ እንዴት ድምፅ እየሰጡ መብታቸው ያስከብሩ እንደነበረ ለማወቅ የሚያስችሉ አንዳንድ አገናኞች (ሊንኮች) ከዚህ በታች ተሰጥተዋል፦

በታሪክ ውስጥ ሰዎች በየቀኑ እንዴት ድምፅ እየሰጡ መብታቸው ያስከብሩ እንደነበረ ለማወቅ የሚያስችሉ አንዳንድ አገናኞች (ሊንኮች) ከዚህ በታች ተሰጥተዋል፦

የአሜሪካ ኅብረተሰባዊ እንቅስቃሴዎች ፕሮጄክትን በቦታ ለይቶ ማስቀመጥ

Futurity Mapping Project

የአሜሪካ የሲቪል መብቶች እንቅስቃሴ፣ 1919-1968

ዚን (Zinn) የትምህርት ፕሮጄክት